ሰላም፣ ኢዮብ እባላለሁ።
የሩትስ ዲዛይን እና ህትመት መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ
ግራፊክ ዲዛይነር ነኝ፤ ማተሚያ ቤቱንም የምመራው እኔው ነኝ። ሳምንቴ በኮምፒውተሩና በማተሚያው መካከል ይከፈላል፦ ሎጎ ዲዛይን ማድረግ፣ የቀለም ሳምፕል ማረጋገጥ፣ እና ማስታወቂያውን በስክሪኔ ላይ እንዳዩት ግድግዳ ላይም እንዲያምር መከታተል ዋና ስራዬ ነው።

ሩትስ ዲዛይን እና ህትመትን በ2018 ስጀምር፣ ስራዬ በብዛት በቢዝነስ ካርድ እና በቲሸርት ላይ ብቻ ያተኮረ ነበር። ዛሬ ግን ከሰፈር ካፌዎች ጀምሮ እስከ ዩኒሴፍ (UNICEF) ላሉ ትልልቅ ተቋማት ሙሉ የብራንድ ዲዛይኖችን እንሰራለን፤ ባነሮችን እና ሮል አፖችን እናትማለን፤ እንዲሁም ማራኪ የሆኑ የኒዮን እና 3D ማስታወቂያዎችን ኒዮን ላይቶች እናዘጋጃለን።
አንድን ስራ ከጅምሩ እስከ መጨረሻው ከእጄ እስኪወጣ በቅርበት ማጠናቀቅ በጣም ደስ ይለኛል። ምክንያቱም ሎጎዎን ዲዛይን ያደረገው ሰው ራሱ ህትመቱንም ሲቆጣጠረው፣ በኮምፒውተር ላይ ያያችሁት ዲዛይን ምንም ጥራቱ ሳይጓደል ልክ እንዳሰባችሁት ሆኖ ሲወጣ ደስ ይላል።
ገና በወረቀት ላይ የተጫረ ሀሳብ ብቻ ያላችሁ የካፌ ባለቤትም ብትሆኑ፣ ለቀጣዩ ሳምንት 500 ቲሸርቶች በአስቸኳይ የምትፈልጉ የድርጅት ሃላፊዎች ፤ በማንኛውም ሰዓት ብታናግሩኝ በደስታ እቀበላችኋለሁ።
ሀሳብዎን አብረን ወደ እውን እንቀይረው!
Beyond your paid
ከከፈሉት በላይ። ስራው እኛ እስክንረካበት ድረስ አናስረክብም፤ ቃል የገባነውን ቀን እንጠብቃለን።