አማ
ዋጋ ይጠይቁ
መነሻ / አገልግሎቶች / ቲሸርትና ኮፍያ

የቲሸርትና የኮፍያ ህትመት በአዲስ አበባ

ለዝግጅት፣ ለቤተክርስቲያን፣ ለትምህርት ቤትና ለድርጅት የሚሆኑ ቲሸርቶች፣ ፖሎዎችና ኮፍያዎች። ፊትና ጀርባ፣ በማንኛውም ቀለም።

1–5ቀን
5+ዝቅተኛ ብዛት
DTFስክሪን · ጥልፍ
Proof · rootsprint.art
የምንሰራቸው

የህትመት አይነቶች

የትኛው ለስራዎ እንደሚሻል እንመክርዎታለን፤ በብዛቱ፣ በቀለሙ ብዛትና በጨርቁ ይወሰናል።

DTF ህትመት

ብዙ ቀለም ላላቸው ዲዛይኖችና ለትንሽ ብዛት፤ ጥርት ያለና የማይለቅ።

ስክሪን ፕሪንት

ለብዙ ብዛትና ለጥቂት ቀለሞች፤ በአንድ ፍሬ ዋጋው ይቀንሳል።

ጥልፍ

ለኮፍያ፣ ለፖሎና ለዩኒፎርም ሎጎ፤ ረጅም እድሜ ያለው።

ፖሎና ዩኒፎርም

ለሰራተኞችና ለሆቴሎች የሚሆኑ፣ በድርጅትዎ ቀለም።

ዝርዝር መረጃ

ብዛት፣ ጨርቅና ጊዜ

ዋጋው በብዛቱ፣ በህትመት ቦታዎቹና በቲሸርቱ አይነት ይወሰናል።

ምርትጨርቅብዛትጊዜ
ቲሸርት100% ጥጥ ወይም ፖሊስተር5 – 5,0001–5 ቀን
ፖሎፒኬ ጥጥ10 – 2,0005–10 ቀን
ኮፍያጥጥ ትዊል20 – 2,0005–10 ቀን
ሁዲና ጃኬትፍሊስ10 – 1,0007–12 ቀን
የሰራናቸው

ቲሸርትና ኮፍያ

ፎቶዎቹ ሁሉም በቡድናችን የተሰሩ ስራዎች ናቸው።

We Will Worship
ፊትና ጀርባ ህትመት
Prayer Walk
John 3:16
Big Smile Africa
የድርጅት ፖሎዎች
በብዛት የታተመ
Sofi Malt
በሁሉም ቀለም
ጥያቄዎች

ብዙ ጊዜ የሚጠየቁ

የቲሸርት መጠኖች (size) ይቀላቀላሉ?

አዎ፤ ከS እስከ 3XL ድረስ በአንድ ትዕዛዝ ውስጥ መቀላቀል ይችላሉ።

ቲሸርቱን እኔ ማምጣት እችላለሁ?

አዎ፤ ጨርቁን ካየን በኋላ የትኛው የህትመት አይነት እንደሚሻል እንነግርዎታለን።

ህትመቱ በእጥበት ይለቃል?

አይለቅም። ቲሸርቱን ገልብጠው በቀዝቃዛ ውሃ እንዲያጥቡት እንመክራለን።